Luke 24:49-51

Amharic(i) 49 እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ። 50 እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። 51 ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።