Luke 3:10-14

Amharic(i) 10 ሕዝቡም። እንግዲህ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። 11 መልሶም። ሁለት ልብስ ያለው ለሌለው ያካፍል፥ ምግብም ያለው እንዲሁ ያድርግ ይል ነበር። 12 ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው። መምህር ሆይ፥ ምን እናድርግ? አሉት። 13 ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው። 14 ጭፍሮችም ደግሞ። እኛ ደግሞ ምን እናድርግ? ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም። በማንም ግፍ አትሥሩ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፥ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ አላቸው።