Amharic(i) 19 እርሱም። በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። 20 ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት። 21 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም። 22 እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።