Mark 1:12-13

Amharic(i) 12 ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው። 13 በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ፥ መላእክቱም አገለገሉት።