Matthew 24:15-17

Amharic(i) 15 እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥ 16 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ 17 በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፥