Mark 7:20-23

Amharic(i) 20 እርሱም አለ። ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ያ ነው። 21 ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፥ 22 ዝሙት፥ መስረቅ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ መጐምጀት፥ ክፋት፥ ተንኰል፥ መዳራት፥ ምቀኝነት፥ ስድብ፥ ትዕቢት፥ ስንፍና ናቸውና፤ 23 ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።